EthiopiaNews

ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚቀርቡት ስምንቱ አጀንዳዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ ድምፅ፣ ቅሬታ እና ስጋት የተቀዱ መሆኑ ተገለፀ።

ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚቀርቡት ስምንቱ አጀንዳዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ ድምፅ፣ ቅሬታ፣ ፍላጎት፣ ተስፋና ስጋት የተቀዱ ናቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላለፉት አራት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያና ከሀገር ውጭ ጭምር በመንቀሳቀስ፣ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ዜጎችን በማማከርና በማወያየት የሰበሰባቸውንና ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ግብአት የሚሆኑ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎችን ትናንት ይፋ አድርጓል።

የተቋሙ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ዘላቂ ሰላም፣ ሀገራዊ መግባባት እና የጋራ እጣ ፈንታን በጋራ መበየን እጅግ አስፈላጊ በሆነበት ታሪካዊ መንገድ ላይ ትገኛለች።

ሂደቱ ተዐማኒና ሁሉንም ማህበረሰብ ያካተተ እንዲሆን ለማድረግም በሁሉም ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ሰፊ የህዝብ ምክክር መካሄዱንም ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv