ኢትዮጵያን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት የተዘጋጀው የዕዳ ሽግሽግ ሥርዓት ቀልጣፋ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት የተዘጋጀውና የጋራ ማዕቀፍ በመባል የሚታወቀው የዕዳ ሽግሽግ ሥርዓት ቀልጣፋ እንዲሆን የሚያስችል ማሻሻያ እንዲደረግ አበዳሪ አገራትን የሚያስተባብረው የፓሪስ ክለብ አሳስቧል፡፡
ቡድኑ ባወጣው የ2025 ዓመታዊ ሪፖርቱ ይህንኑ የገለጸ ሲሆን የኢትዮጵያን የተጓተተ የዕዳ ድርድር በማሳያነት በማንሳት በማዕቀፉ ውስጥ ያሉት መዋቅራዊ ክፍተቶች እና በአበዳሪዎች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ስምምነት ላይ እንዳይደረስ ማድረጉን አስፍሯል፡፡
ሪፖርቱ ጨምሮም ከአውሮፓውያኑ 2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ 52 በመቶ የሚሆኑት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት በዝቅተኛና መካከለኛ የዕዳ ጫና ስጋት ውስጥ እንደሚገኙና ቀሪዎቹ 48 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አሁን ላይ ዕዳቸውን መክፈል በማይችሉበት ደረጃ ላይ ይገኛሉም ብሏል፡፡
ቻድ፣ ዛምቢያ እና ጋና በጋራ ማዕቀፉ ስር የዕዳ ሽግሽጋቸውን በአብዛኛው ማጠናቀቅ ቢችሉም ኢትዮጵያ ግን 1 ቢሊዮን ዶላር በሚገመተውና ባልከፈለችው የዩሮ-ቦንድ ዕዳ ምክንያት በግል ቦንድ ባለሀብቶች እና በይፋዊ አበዳሪዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ሽግሽጉ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
