በትግራይ የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፉ ሀይሎች የአፍሪካ ህብረት ለጀመረው የውይይት ጥረት ሊሳተፉ እንደሚገባ የአሜሪካ ኤምባሲ ጥሪውን አቀረበ።
በትግራይ የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፉ ሀይሎች የአፍሪካ ህብረት ለጀመረው የውይይት ጥረት ሊሳተፉ እንደሚገባ የአሜሪካ ኤምባሲ ጥሪውን አቀረበ።
ኤምባሲው ይሄን ያለው በትግራይ ያለውን የፖለቲካ እና የሰብአዊ ድጋፍ ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን ባሳወቀበት መግለጫ ላይ ነው።
ኤምባሲው የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማኅበራት መሪዎች የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርቧል።
ኤምባሲው በትግራይ የሰብአዊ ድጋፍ እንዲቀርብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጾ በትግራይ ዘላቂ ሰላም መኖሩ ክልሉ ከእለት ደራሽ እርዳታ እንዲወጣ እና ችግሮችን በዘላቂነት እንዲፈታ ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብሏል።
አሜሪካ የትግራይ ህዝብን እንደምትደግፍ በመግለጫው ተጠቅሷል። መረጃው ከአሜሪካ ኤምባሲ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
