EthiopiaNews

በ11 ወራት የአስተዳደር በደል ተፈጽሞብናል ያሉ ከ44 ሺህ በላይ ዜጎች ከ1,700 በላይ አቤቱታዎችን አቅርበዋል ተብሏል።

ባለፉት 11 ወራት የአስተዳደር በደል ተፈጽሞብናል ያሉ ከ44 ሺህ በላይ ዜጎች ከ1ሺህ 700 በላይ አቤቱታዎችን ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታውቋል።

እንባ ጠባቂ ተቋም ይህንን ያሳወቀው ትላንት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረበው  የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ላይ ሲሆን ከቀረቡት ውስጥ አንድ ሺ 437 አቤቱታዎች በመንግስት ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸዉ ብሏል።

ቅሬታ ካቀረቡ ዜጎች መካከል 82 ሰራተኞች ወደ ስራ እንዲመለሱ፣ 1 ሺህ 319 ሰራተኞች ደግሞ የደረጃ እድገትና ዝውውር እንዲያገኙ፣ 36 ሚሊዮን ብርና ጥቅማጥቅም እንዲከፈላቸው መደረጉን ጠቁሟል።

እንዲሁም የመሬት ካሳ ላልተሰጣቸው 41 ዜጎች 36 ሺህ ካሬ ሜትር ካሳ መሬት እንዲያገኙ፤ 106 ዜጎች ደግሞ የጡረታ መብታቸው ተከብሮ ያልተከፈለ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው መደረጉን በሪፖርቱ ገልጿል።

በተመሳሳይ አንድ ሺህ 196 አቤቱታ አቅራቢዎች ደግሞ ከህግ አግባብ ውጪ እንዳያገኙ ተከልክለው የነበሩ መንግስታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉንም ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ አሳውቋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews