InternationalNews

በቬኑዙዌላ ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 235 ሲደርስ 4 ሺህ 300 ቆስለዋል።

በቬኑዙዌላ በደረሰው ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 235 ሲደርስ ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ በርካታ ሰዎች ደግሞ የገቡበት አልታወቀም ተብሏል፡፡

በዚህ ከባድ ርዕደ መሬት የቆሰሉ ሰዎች ቁጥርም ወደ 4 ሺህ 300 ማሻቀቡ ሲነገር በሀገሪቱ መዲና ካራካስ እና በባህር ዳርቻዋ ላጉያራ ከተሞች በደረሰው በዚህ ርዕደ መሬት ከፈራረሱ ህንፃዎች ውስጥ አሁንም የድረሱልን ድምፆች እየተሰሙ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከፈራረሱት በርካታ ህንፃዎች ስር በህይወት ያሉ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም የአደጋው ግዝፈት የነፍስ አድን ስራውን ፈታኝ እንዳደረገው እየተገለጸ ይገኛል፡፡

በሁለቱ ከተሞች ከመፍረስ የተረፉት ህንፃዎችም ቢሆኑ ለደህንነት አስጊ በመሆናቸው ብዙ ሰዎች በየመንገዱ ለማደር መገደዳቸው ሲነገረ ሌሎች በርካቶች ደግሞ መኖሪያ ቤታቸው መፈራረሱን ተከትሎ ጎዳና መውጣታቸው ተሰምቷል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews