የግብርና ሚኒስቴር ለ2018/19 የምርት ዘመን 20.9 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ፈፀመ።
የግብርና ሚኒስቴር ለ2018/19 የምርት ዘመን 20 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ መፈፀሙን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ለ2018/19 የምርት ዘመን ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታሉ ወደብ የደረሰ መሆኑን ገልጸው 12 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታሉ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ በቀን እስከ 200 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች ማዳበሪያውን ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ እያጓጓዙ መሆኑን ጠቅሰው በዚህም በአማካይ በቀን 10,000 ሜትሪክ ቶን እያጓጓዙ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
ከባለፈው ዓመት የከረመውን የአፈር ማዳበሪያ ጨምሮ እስካሁን በአጠቃላይ 19 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለ2018/19 የምርት ዘመን ለስርጭት የቀረበ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታዋ ከዚህ ውስጥ 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታሉ ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል ብለዋል። መረጃው ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
