ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን አስመረቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 87.6 ሄክታር መሬት የሚሸፍነውን እና 10.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን ትናንት በይፋ አስመረቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ሰፊ መሰረተ ልማት የወንዝ መከላከያ ግንቦችን፣ ዘመናዊ ድልድዮችን እና ሰፊ አረንጓዴ ስፍራዎችን በጋራ የያዘ መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱ የግንባታ ስኬት ብቻ ሳይሆን መዲናችንን የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋምና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች፣ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ስልታዊ ሽግግር የሚያፋጥን ታላቅ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ 1 ትልቅ ግድብ፣ 16 አነስተኛ ግድቦች፣ 3 ቼክ ዳሞች፣ 1.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሃይኪንግ፣እንዲሁም 20.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የወንዝ ድጋፍ ግድግዳን ያካተተ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
