EthiopiaNews

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጥ የአየር ጭነት አጓጓዥ አየር መንገድ በመባል ተሸላሚ መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ እና የሎጂስቲክስ አገልግሎት በ2026ቱ የእስያ ጭነት፣ ሎጂስቲክስ እና አቅርቦት ሰንሰለት የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የአፍሪካ ምርጥ የአየር ጭነት አጓጓዥ አየር መንገድ በመባል ተሸላሚ መሆኑን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ በባለድርሻ አካላት እና በደንበኞች ድምፅ አሸናፊዎች የሚመረጡበትን ይህን ሽልማት በማግኘቱ ታላቅ ደስታ እንደተሰማው ገልፆ ይህን ስኬት ዕውን እንዲሆን ላስቻሉ አጋሮቹ፣ ደንበኞቹ እንዲሁም ሰራተኞቹ ምስጋናውን አቅርቧል።

አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ መሰረተ ልማቶች፣ ስልታዊ ጥምረቶች፣ እንዲሁም አዳዲስ የሎጂስቲክስ አሰራሮች በመታገዝ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ እና የንግድ ግንኙነቶችን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

አየር መንገዱ በአመት ከ850 ሺ ቶን በላይ የካርጎ ጭነት እንደሚያጓጉዝ መረጃዎች ያመለክታሉ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews