EthiopiaNews

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ሞሐሙድ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ ገቡ።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ሞሐሙድ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ ገቡ።

ፕሬዚዳንቱ ትናንት አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ፣ በንግድ ፣ በኢኮኖሚ ትብብር ፣ በፀጥታ እና በቀጠናዊ የፀጥታ ጉዳዮች ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሀገሪቱ መንግስት ገልጿል።

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ከማድረጋቸው አስቀድሞ ከጅቡቲ አቻቸው እስማኤል ኦማር ጉሌህ ጋር በጅቡቲ መምከራቸውን ቪላ ሶማሊያ አስታውቋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews