ብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራምን ሶስተኛ ምዕራፍ ለመተግበር 18 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ፡፡
ዘላቂና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይልን በሁሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂ እየተዘጋጀ እንደሆነ የገለጸው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለዚህ ተግባርም ከ18 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ አሳውቋል፡፡
ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው ብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት በተካሄደበት ወቅት ሲሆ በመድረኩ የግሉ ዘርፍም ተሳትፎ እንዲያድግ የሚያግዝ የኢነርጂ ፖሊሲ ክለሳ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ ታዳሽ፣ ዘላቂና አስተማማኝ የኃይል ተደራሽነት የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ተገልጾ በኢትዮጵያ የኃይል አማራጭ ምንጮች ለመጠቀምና ማመንጨት አቅምን ማሳደግ ለማሻሻል ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አክሎ አስታውቋል።
ከ18 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ የተገለጸው የዚህ እቅድ የሦስተኛው ምዕራፍ ትግበራም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ንጹሕ ኢነርጂን ማስፋፋት፣ ለምርታማነት ተግባራት ቅድሚያ መስጠትና የዘርፉን ዲጂታላይዜሽን አሠራር ማጠናከር ላይ የሚያተኩር መሆኑን ተነግሯል።
በመርሐ ግብሩ ትግበራ እስከ 2035 ድረስ ባሉት ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይልን በመላ አገሪቱ ለማዳረስ መታቀዱም ተገልጿል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
