EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ80 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከ272 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።

ባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተገኘው የትርፍ መጠን ካለፈው  በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የ146.3 በመቶ ብልጫ ያለው ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ባንኩ አዲስ በተጀመረው በጀት ዓመት 120 ቢሊዮን ብር ትርፍ ለማግኘት ማቀዱን ተናግረዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews