የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ ጣሊያን የውጭ የስራ ስምሪት ሊጀመር መሆኑን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያስታወቀው በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ ጣሊያን ለሚደረገው የስራ ስምሪት ኘሮግራም እንዲመዘገቡ ጥሪ ባቀረበበት መግለጫ ነው።
ሚኒስቴሩ በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በጣሊያን በሆቴልና መስተንግዶ ዘርፍ የሰው ኃይል እንደሚፈለግ ገልጾ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ሀገሪቱ ሄደው መስራት የሚፈልጉ አመልካቾች እንዲያመለክቱ ጥሪውን አቅርቧል።
ምዝገባም ሆነ ስምሪት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ ብቻ የሚከናወን የገለፀው ሚኒስቴሩ ለየትኛውም አካል ውክልናም ሆነ ፈቃድ አለመስጠቱን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ አመልካቾች በአቅራቢያቸው ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ እንዲሰጡ እና የሰራተኛነት መለያ ቁጥር እንዲይዙ ጥሪውን አስተላልፏል። ዝርዝር መረጃውን ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ማግኘት ይችላሉ፡፡
https://www.facebook.com/share/18S5qqTz6G/
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
