InternationalNews

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ጠይብ ኤርዶሀን የጦርነት ሱስ አለበት ያሉት የእስራኤል መንግስት ቀጠናውን ወደ ብጥብጥ እንዳይከተው ሊደረግ ይገባል አሉ።

ኤርዶሀን የእስራኤል መንግስት የአሜሪካና ኢራን ስምምነት እንዳይረጋ ጥረት እያደረገ መሆኑን በቅርብ እናውቃለን በዚህ በኩልም ፍላጐቱ ሊሳካ አይገባም ብለዋል።

በቀጠናውም የባሩድ ሽታና ደም መፍሰስ ዳግም እንዳይታይ በርትተን እንሰራለን ነው ያሉት።

ኤርዶሀን ይሄን ያሉት አሜሪካና ኢራንን ያደራደረችው ፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሸሪፍን ተቀብለው ካነጋገሩ በኋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት አገራቸው ማየት የምትፈልገው ሰዎች በሃይማኖታቸው ወይም ዘራቸው ምክንያት በደል የማይደርስባቸው መካከለኛው ምስራቅን ነው ብለዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews