EthiopiaNews

ይህ ጥሪ ትናንት በአዲስ አበባ በተካሄደው የብሪታንያ የንግድ ማበረታቻ እንዲገነዘቡ ባለመ የሥልጠና መድረክ ላይ የተላለፈ ሲሆን የኢትዮጵያ ላኪዎች የዕድሉን፣ የመስፈርቶቹንና የተግባራዊ ሂደቶቹን ግንዛቤ እንዲያሳድጉ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ስልጠናው በብሪታንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፣ በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፣በብሪታንያ ኤምባሲ እና በሌሎች አጋር አካላት የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን ቡና፣ የግብርና ምርቶችና ጨርቃጨርቅ ብሪታንያ ባመቻቸችው የሃገራት የንግድ ማበረታቻ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ የወጪ ንግድ ዘርፎች ናቸው ብለዋል።

የብሪታንያ የንግድ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ጀማል ሁሴን ብሪታንያ በተወሰኑ ምርቶች ላይ ለታዳጊ ሀገራት ያመቻቸችው የንግድ ማበረታቻ አተገባበርን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ እና የብሪታንያ አጠቃላይ የንግድ ልውውጥ በፈረንጆቹ 2025 አመት 462.3 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ።መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።