InternationalNews

ቢቢሲ እንደዘገበው የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ፈርመውበታል በተባለ ሀሰተኛ ደብዳቤ በግዙፉ የፕሬዝዳንቱ ህንጻ ውስጥ የባህር ማዶ እንቅስቃሴ ማበልጸጊያ የተባለ የሀሰት መስሪያ ቤት ቢሮ እንዲሰጠውና የመንግስት 1 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንዲደረግለት ሆኗል።

ፖሊስ ጉዳዩን ከደረሰበት በኋላ ሀሰተኛውን ደብዳቤ ያዘጋጀውና የጽህፈት ቤቱ ዳይሬክተር ነኝ የሚል አንድ ግለሰብ ከመኖሪያው መሰወሩ ተገልጿል።

ጽህፈት ቤቱን እስከመፈጠሩ የማያውቁት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒቡ የሀገሪቱ የጸር ሙስና ኮሚሽን ጉዳዩን እንዲያጣራ ትእዛዝ ሰጥተዋል።