EthiopiaNews

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር ) የተደረሰው ስምምነት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ስትራቴጂካዊ እመርታ ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ ስምምነቱ በሸቀጦችና በአገልግሎት ዘርፎች ላይ በጋራ የተደረሱ የገበያ ተደራሽነት ግዴታዎችንና ጥቅሞችን ያካተተ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት ከታይላንድ በተጨማሪ ከቻይና፣ ከሩሲያ፣ ከአርጀንቲና፣ ከቱርክ፣ ከብራዚል፣ ከጃፓን፣ ከሕንድ እና ከኒውዚላንድ ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ስምምነቶች መፈራረሟ የሚታወቅ ነው። መረጃው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።