EthiopiaNews

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ይሄን ያለው በኦሮሚያ ክልል የ3ኛው ዙር የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታት ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ከሰኔ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ በቢሻን ጉራቻ እና በአምቦ ሰንቀሌ ጊዜያዊ ማዕከላት ከ5 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላለቁ ተደርጓል ብለዋል።

ኮሚሽነሩ በኦሮሚያ ክልል ወደ ማህበረሰቡ የተቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎች ቁጥር ከ12 ሺህ በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ95 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን ገልፀዋል፡፡