InternationalNews

ድርጅቱ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት የዓለም ኢኮኖሚ አማካይ ዕድገት 3 ነጥብ አንድ በመቶ ያድጋል ቢልም አሁን ባወጣው ትንበያ አማካይ ዕድገቱ 3 ከመቶ ብቻ ነው ብሏል።

ተቋሙ የዕድገት ትንበያውን በዜሮ ነጥብ አንድ በመቶ የቀነሰው በኢራኑ ጦርነት ሳቢያ የዓለም ነዳጅና ማዳበሪያ አቅርቦት በእጅጉ በመስተጓጐሉ የበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ጉዳት ይደርስበታል በሚል ነው።

እንደውም የኢኮኖሚ ዕድገቱ በጣም ያልተጐዳው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የሚፈሰው መዋዕለ ንዋይ በጣሙን በማደጉ ነው ይላል።

አይ ኤም ኤፍ በፈረንጆቹ 2027 ግን የዓለም ኢኮኖሚ አንሰራርቶ 3 ነጥብ አራት በመቶ ያድጋል ማለቱን አልጀዚራ ዘግቧል።