በሶማሌ ክልል ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ ትናንት በደረሰ የመኪና አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ እና 3 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ መድረሱ ተነገረ።
አደጋው የተከሰተው በአንድ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና በአይሱዙ ጭነት መኪና መካከል በተፈጠረ ግጭት መሆኑን የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የአደጋው መንስኤ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ እየተጣራ እንደሚገኝ ገልጿል።
የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ ሙሐመድ በአደጋው ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን የገለጹ ሲሆን፣ ለተጎጂ ቤተሰቦችም መጽናናት ተመኝተዋል።መረጃው ከሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።
