ጨፌ ኦሮሚያ የክልሉን የ2019 በጀት ዓመት ያፀደቀው በመካሄድ ላይ ባለው 6ኛው ጨፌ 5ኛ የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤው ነው።
ጨፌው ለክልል ስራ ማስኬጃ ወጪዎች ከ80 ቢሊዮን 220 ሚሊዮን በላይ ብር እና ለክልል የካፒታል ወጪ ደግሞ ከ162 ቢሊዮን 670 ሚሊዮን በላይ ብር እንዲውል አፅድቋል።
ለወረዳዎች እና ለከተሞች አስተዳደር የሚደረግ ድጋፍ ከ459 ቢሊዮን 109 ሚሊዮን በላይ ብር እና ለክልል ተጠባባቂ በጀት ሁለት ቢሊዮን ብር ሆኖ እንዲውል ጨፌው ማፅደቁ ነው የተነገረው፡፡
የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በ2019 በጀት ዓመት 520 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸዋል።
