InternationalNews

ምርመራው የተጀመረውም ኢትዮጵያ ገጣጥማ የምትልካቸው ሶላር መሳርያዎች ከአሜሪካ ጋር የንግድ ውድድር ካለባት ቻይና በሚገኙ ጥሬ እቃዎች የተፈበረኩ ናቸው በሚል ነው፡፡

የፀሐይ ኃይል ኢንዱስትሪ መረጃ ምንጭ የሆነው ሶላር ፓወር ወርልድ እንደዘገበው ፣ ከሐምሌ 2025 በፊት  በአሜሪካ  ያልተለመዱት ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የፀሐይ ኃይል መሣሪያዎች፣ በ2025 ሁለተኛ አጋማሽ ወደ 277 ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ ደርሰው በ2026 ሽያጫቸው እያደገ መጥተዋል ብሏል።

ምርመራው የተጀመረው የአሜሪካ የሶላር አምራቾች በቻይና የተመረቱ የሶላር ምርቶች በአሜሪካ የተጣለባቸውን ታሪፍ ለማለፍ በኢትዮጵያ በኩል ኤክስፖርት እየተደረጉ ነው የሚል ቅሬታ መቅረባቸውን ተከትሎ ነው።

ቅሬታውን በግንቦት ወር ያቀረቡት ፈርስት ሶላር እና የደቡብ ኮሪያው ሐንዋ ግሩፕ ቅርንጫፍ የሆነው ኪውሴልስ  ጨምሮ ስምንት የአሜሪካ የፀሐይ ኃይል አምራች ኩባንያዎች መሆናቸው ዘገባው አመልክቷል።