ለዚህ እቅድ መሳካት የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በቂ እንክብካቤ ወሳኝ መሆኑን ያነሱት የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በጉራፈርዳ እና በደቡብ ቤንች ወረዳዎች የሚገኘውን የባበቃ ቡና ልማት ድርጅትን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
ድርጅቱ ካለው 10 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ 5 ሺህ 677 ነጥብ 64 ሄክታሩ በቡና የተሸፈነ ሲሆን፣ ልማቱም በበቂ እንክብካቤ እና በቴክኖሎጂ ተደግፎ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ከፍተኛ ጥራት እና ዋጋ ያለው ቡና ለማምረት በሳይንሳዊ አሠራር ላይ የተመሰረተ እንክብካቤ ማድረግ ወሳኝ ስለመሆኑም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡
ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ኤክስፖርት 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ በማስገኘት አዲስ ታሪክ ማስመዝገቧን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ ይህ ስኬት የተመዘገበው ከቡና ምርት እስከ ዝግጅት እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ገበያ እስከማቅረብ ድረስ በተሠራው የተቀናጀ ሥራ እና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በፈጠረው ምቹ ሁኔታ መሆኑን አስታውቀዋል።
