EthiopiaNews

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተቋማዊ ለውጥን በመምራት እና ለወጣቶች ዕድሎችን በማስፋፋት ዕውቅና ከተሰጣቸው አምስት የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ሆኖ መመረጡን ገልጿል።

ሽልማቱ በምርምር፣ በፈጠራ፣ በሰው ኃይል ልማት እና በማህበረሰብ ተፅዕኖ ላይ የሚደረገውን ሥራ የበለጠ ለማጠናከር የሚረዳ የ3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍን ያካተተ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ይህ ታላቅ ዕውቅና ሪኢማጅኒንግ አወር ፊዩቸር ብለን ከሰየምነው ስትራቴጂክ ዕቅዳችንን እና ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር ያለንን የረጅም ጊዜ አጋርነት የሚያንፀባርቅ ነው ብሏል።

እንደ ኢትዮጵያ አንጋፋ፣ ስመ-ጥር እና ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ዕድል ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ የሚሆን የምርምር ብቃት፣ ፈጠራ እና ለውጥ አምጪ ትምህርትን ለማጠናከር እንደሚጠቀምበት ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ ላደረጉ መምህራኖች፣ ሰራተኞች፣ የአሁኖቹና የቀድሞ ተማሪዎቹ እና አጋሮቹ አመስግኗል።መረጃው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ ነው።