EthiopiaNews

የጤና ሚኒስቴር ይሄን ያለው የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ተመዛኞች ባቀረበው ጥሪ ነው።

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ የጤና ባለሙያዎች በነሀሴ ወር 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ሙያ ፈቃድ መረጃዎቻቸውን እያስተሳሰሩ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

እስካሁን ድረስ መረጃዎቻቸውን ወደ ሲስተም ያላስገቡ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች እስከ ሃምሌ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ መረጃዎቻቸውን በዚህ ሊንክ https://hple.moh.gov.et/ እንዲያስተሳስሩ ጠይቋል።

ተመዛኞች የብሄራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት እንዲመዘገቡ ጥሪ ያቀረበው ሚኒስቴሩ የተጀመረው መረጃን የማስተሳሰር ሂደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሂደት እንደሚቀጥልም ነው የገለጸው፡፡ መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።