EthiopiaNews

ተመካካሪዎቹ በንኡሳን ቡድኖች ተከፋፍለው በተመደቡበት አጀንዳ ላይ መመካከር የጀመሩት ከትላንት በስቲያ ሲሆን የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይፋ ባደረገው መረጃ ተመካካሪዎች በትላንትናው እለትም  በየቡድናቸው በመሆን ምክክሩ መቀጠሉን ተናግሯል፡፡

እያንዳንዳቸው 50 ተመካካሪዎችን በመያዝ በ80 ቡድን ተከፋፍለው መመካከር የጀመሩት ንዑሳን ቡድኖች በተሟላ ሁኔታ ከትላንት በስቲያ ከሰዓት ጀምሮ በየንዑስ ቡድናቸው አስር አስር በመሆን እየመከሩ የሚገኙ ሲሆን ይህ ሂደት ዛሬም የሚቀጥል ይሆናልም ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት፣ ከተለያዩ የሙያ ማህበራት፣ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ እና ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተውጣጡ ከ50 በላይ ገለልተኛ ታዛቢዎችም የምክክር ሂደቱን እየታዘቡ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡