EthiopiaNews

የህክምና ኮሌጁ ለአንድ ሳምንት የቆየ ነጻ የጤና ምርመራ መርሃ ግብር ማካሄዱን የገለጸ ሲሆን የደም ግፊት፣ የስኳር፣ የልብ በሽታ፣ የጡትና የማህፀን በር ካንሰር፣ የማህፀንና ፅንስ፣ የቀዶ ሕክምናን ጨምሮ የዓይን፣ የጥርስ እና ሌሎች ሕክምናዎችን በነጻ ሲሰጥ ቆይቷል።

ሁሉም ሰው ዓመታዊ የጤና ምርመራ የማድረግ ልማድ ሊኖረው ይገባል ያለው ኮሌጁ በተጨማሪም እድሜ እና ጾታን መሠረት አድርገው በየአመቱ እና በየወቅቱ ሊደረጉ የሚገቡ የምርመራ አይነቶች እንዳሉ ገልጾ አስቀድሞ የጤና ምርመራ ማድረግ በበሽታ ከመያዝና ከመጎዳት ያድናል ሲል ተናግሯል።

ሆስፒታሉ ከሐምሌ 7 ጀምሮ ነፃ ህክምናን ሲሰጥ የቆየ ሲሆን የታካሚዎች ቁጥር ከተጠበቀው በላይ በመጨመሩ እና ማህበረሰቡ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ሆስፒታሉ የዘንድሮውን የክረምት በጎ ፍቃድ ነፃ ምርመራ አገልግሎት እስከ ሀምሌ 17 ማራዘሙን አስታዉቋል፡፡