ይህ የተነገረው የኦፕታሲያ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳልቫዶር አንግላዳ ሴማፎር ለተሰኘው የሚድያ ተቋም በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ነው።
ኦፕታሲያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በተለይ የባንክ ተደራሽ ላልሆኑ ዜጎች እና ለአነስተኛ ድርጅቶች ብድር የሚያቀርብ ነው ተብሏል።
ኩባንያው በፈረንጆቹ 2025 በ38 ሃገራት ላሉ ተጠቃሚዎች 6 ቢሊየን ዶላር ብድር መስጠቱ የተገለጸ ሲሆን ከኢትዮጵያ ባሻገር በግብፅ ገበያ ለመግባት ማቀዱም በዘገባው ተጠቅሷል።
