EthiopiaNews

ብሔራዊ ባንክ ይሄን ያስታወቀው በፈረንጆቹ 2026/27 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት የሚያካሂደውን የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ መርሃ ግብር ትናንት ይፋ ባደረገበት መግለጫ ላይ ነው።

በዚህም በፈረንጆቹ ኦገስት 12 ፣ኦገስት 26 ፣ ሴፕቴምበር 9 እና ሴፕቴምበር 23 2026 አመት ለሚደረገው የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ለእያንዳንዱ ቀን አንድ መቶ ሃያ አምስት ሚሊየን ዶላር መመደቡን ባንኩ ገልጿል።

ብሔራዊ ባንክ ከፈረንጆቹ ኦገስት 12 2026 አመት ጀምሮ በየሁለት ሳምንት የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያደርግ አስታውቋል።መረጃው ከብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው።