እስካሁን ከቀረቡ 47ሺ የሚጠጉ የአክሲዮን ግዢ ጥያቄዎች ውስጥ 96 በመቶ የሚሆኑት አክሲዮኖች የባለቤትነት ማረጋገጫ እንደተሰጣቸውም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ይህንን ያስረዱት የተቋማቸውን አመታዊ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት 215 ነጥብ 82 ቢሊዮን ብር ገቢ በማግኘት ዓመታዊ ዕቅዱን 99 ነጥብ 7 በመቶ ማሳካቱንም ተናግረዋል፡፡
የኩባንያው ይኸው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ33 ነጥብ 2 በመቶ ብልጫ ያለው ዕድገት የተመዘገበበት ነውም ብለዋል።
ለተመዘገበው ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ ካበረከቱ የአገልግሎት ዓይነቶች መካከል ዋናዎቹ የዳታ እና ኢንተርኔት አገልግሎት 31 ነጥብ 1 በመቶ፣ የሞባይል ድምፅ አገልግሎት 23 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝም ተናግረዋል፡፡
