የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት እና የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
ቶኒ ብሌየር የሰው ሰራሽ አስተውሎት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን እያዘመነ ስለመሆኑ በመናገር ተቋማቸው ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ሙሉ ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን መርሃ ግብር ለመደገፍ እያደረገ ላለው አበርክቶ አመስግነዋል።
ሁለቱ ተቋማት በኢትዮጵያ ያለውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ልማት እና ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ በጋራ እንደሚሰሩም ተገልጿል።መረጃው ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት የተገኘ ነው።
