ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለዚሁ ጉዳይ በሰጡት ማብራሪያ በሀገራቸው እንዳይንቀሳቀስ የታገደ የኢራን ገንዘብ መኖሩን ጠቁመው ቴህራን ጉዳት ለምታደርስበት ማናቸውም መርከብ ከዚሁ ገንዘብ ላይ ካሳ እንዲከፈለው እናደርጋለን ብለዋል፡፡
የዚህ ካሳ ክፍያ መጠንም ከፍተኛ እንደሚሆን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቢናገሩም የኢራኑ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ይህንን የትራምፕ ዛቻ ፍትሀዊ ያልሆነና ውጥረቶችን የሚያባብስ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለ13ኛ ተከታታይ ቀን በኢራን ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 4 ሰዎች መገደላቸውንና 5 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ቴህራን ጠቁማለች፡፡
