InternationalNews

በደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ የተቀሰቀሰውና ለቀናት የቆየው ይህ ሰደድ እሳት አሁን ላይ 8 ሺህ 700 ሄክታር መሬትን በማቃጠል ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ መቀጠሉ ነው የተነገረው፡፡

በዚህ አካባቢ የነበሩ ነዋሪዎችና ቱሪስቶች አብዛኛዎቹ በጀልባዎች ከእሳቱ ማምለጣቸው የተነገረ ሲሆን የእሳት አደጋ ሰራተኞች ሰደድ እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረጉ ነው ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ በስፔን መዲና ማድሪድና በርካታ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት ከቁጥጥር ውጪ መሆኑን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁም ነው የተነገረው፡፡