ማማዱ ጆማ የተባለ ታዳጊ ሲክል ሴል ዲዝዝ የተባለ የደም በሽታ ታማሚ ነበረ የተባለ ሲሆን ፈተና ሲኮርጅ ተይዞ ለእስር ከተዳረገ በኋላ ህመሙ ጠንቶበት ከእስር ቤት ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉ ነው የተነገረው፡፡
የታዳጊው አባት ልጃቸው በእስር ቤት እያለም ሆነ በሆስፒታል በቂ እንክብካቤ በማጣቱ ህይወቱ ማለፉን በመጥቀስ ምርመራ እንዲካሄድ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
በጊኒ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመግባት የሀገሪቱን ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ፈተና ሲኮርጁ ከተያዙ እስር እንደሚጠብቃቸው የተነገረ ሲሆን ይህ ታዳጊም ከስልኩ ሲኮርጅ ተይዞ ከሌሎች መሰል ተማሪዎች ጋር ታስሮ ነበር ተብሏል፡፡
ከሁለት ቀናት ምርመራ በኋላ በኩረጃ ወንጀል የ6 ወራት እስራት ፍርድ ተላልፎበት ወደ ዘብጢያ ከወረደ በኋላ ነበር በእስር ቤቱ ፍርዱን እየተቀበለ እያለ የማይድነው የሲልክ ሴል በሽታ ህመም ገጥሞት ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱ ማለፉ ነው የተሰማው፡፡
