EthiopiaNews

ኮሚሽኑ ካለፈው በጀት ዓመት ወደ ዘንድሮ የተዛወሩ 469 መዛግብትን ጨምሮ በአጠቃላይ ከቀረቡለት ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ መዛግብት ውስጥ በ960ዎቹ ላይ ውሳኔ ለመስጠት አቅዶ በ958 መዛግብት ላይ ውሳኔ ማሳለፋን ገልጿል።

ውሳኔ ከተሰጠባቸው መካከል 757 መዛግብት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የተጠየቀባቸው ሲሆን 37ቱ ለድጋሚ ምርመራ መመለሳቸው ተጠቁሟል።

ለድጋሚ ምርመራ ከተመለሱት 37 መዛግብት ውስጥ ደግሞ በ14 መዛግብት ላይ ውሳኔ የሚያስለውጥ አዲስ መረጃ ባለመገኘቱ ውሳኔው የጸና ሲሆን አራቱ የቀረቡበት አግባብ ታይቶ መሻሻላቸውን አመላክቷል።

እንዲሁም 11ዱ መዛግብት ደግሞ መሻራቸውንና ቀሪ መዛግብት በአሁኑ ወቅት እየታዩ እንደሚገኙ ከፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ያገኘው መረጃ ያመላክታል።