የሀገራዊ ምክክር ተመካካሪዎች በቀደሙት ቀናት በአስር አስር የቡድን አባላት በተወያዩባቸው ንዑሳን አጀንዳዎች ላይ ያነሷቸውን ሃሳቦች በቃለ-ጉባኤ አስፍረው በሃምሳ ለተደራጀው ቡድን ማቅረባቸውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አስታውቋል፡፡
ተመካካሪዎቹ በትናንትናው ዕለት በሚመካከሩበት የአጀንዳ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በባለሙያዎች ቡድን የተለያዩ የምክክር ግብዓቶችን የሚሰጡ ገለፃዎች የተደረገላቸው ተመካካሪዎች ዛሬ በ50 ተደራጅተው ምክክሩን መቀጣላቸው ተነግሯል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሚሽኑ ለአካታችነት እና ለልዩ ፍላጎቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለአካል ጉዳተኛ ተመካካሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡
