መድረኩ በዘመቻና ስምሪት ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ዘመናዊ ስልት መቀየስ የሚያስችል ዕድል መፍጠር ያስችላል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ በቀጣናው ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና ሰላምን በማስፈን ግንባር ቀደም ሚናዋን እየተወጣች መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ብሎም ለዓለም ሰላም እና ደህንነት ያላት ቁርጠኝነት ዘመናትን የተሻገረ ነው ብለዋል በመድረኩ፡፡
የተሟላ የሎጅስቲክ እና ኮሙኒኬሽን ሥርዓትን በማረጋገጥ ሽብርተኝነትን በመከላከልና ሰላምን በማስፈን የተሳካ ተልዕኮ መፈፀሟንም አክለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን፣ የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል እና የሀገራቱ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመከላከያ መሪዎች ታድመዋል።
