የኢኳቶሪያል ጊኒ፣ የካሜሩን ፣የቦትስዋና፣ የኮትዲቫር ፣ የሩዋንዳ ፣የዚምባብዌ፣ የናይጄሪያ እና የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ አዲስ አበባ መግባታቸው ነው የተነገረው።
በጉባኤው ለመሳተፍ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች እና የልዑካን ቡድን አባላትም አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
49ኛው የአፍሪካ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ከነገ ሐምሌ 21 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል።መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
