ከከተማዋ ደቡብ አቅጣጫ ያለው እሳት በተለዋዋጩ አየር ሳቢያ አንዴ ጋብ ሲል ሌላ ጊዜ ደግሞ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው። እሳቱ አሁን ከቦርዶ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደርሷል።
ዛሬ ለሊቱን ንፋሱ ቀዝቀ ማለቱና አነስተኛ ካፊያ ዝናብ የጣለ ቢሆንም ቃጠሎው ግን ተጨማሪ ደን እየበላ ነው።
ነገ ማክሰኞ የአየሩ ሙቀት ወደ አርባ ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚጨምር በመሆኑ ቃጠሎው የበለጠ ወደ ቦርዶ ከተማ እንዳይጠጋ ስጋት ፈጥሯል።
በዚሁ ሳቢያ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ካቢኒያቸውን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።
