InternationalNews

በርንሃም ይሄን ያሉት ዛሬ የዩክሬኑን መሪ ቮሎድሚር ዜሌንስኪን አግኝተው ከማነጋገራቸው በፊት ነው።

ዜሌንስኪ ወደ ለንደን አምርተው ጠቅላይ ሚኒስትር በርንሃምን ለማነጋገር የመጀመሪያው መሪ ይሆናሉ ማለት ነው።

ሁለቱ መሪዎች የብሪታንያ ባህር ኃይል ተቋምን በጋራ የሚጐበኙ ሲሆን በዚህ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር በርንሃም ስቶን ክሎክ የተባለ ዘመናዊ የድሮን መከላከያ ስርዓትን ዩክሬን እንድታመርት የአዕምሯዊ ንብረት ፈቃድ ይሰጧታል ተብሏል።

መሣሪያውን ዩክሬን በብዛት ማምረቷ ራሷን ከሩሲያ የድሮን ጥቃት እንድትከላከል በእጅጉ ያግዛታል ይላል የቢቢሲ ዘገባ።