ይህ የተገለጸው የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ዓመታዊ የምክክር መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡
በመድረኩ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ በተጠናቀቀው በ2018 የበጀት ዓመት ከግብር 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 518 ትሪሊየን ብር በመሰብሰብ ከእቅድ በላይ ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት፡፡
የታክስ መሠረትን ከማስፋትና አስተዳደሩን በማሻሻል በበጀት ዓመቱ አዎንታዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን የገለፁት ሚኒስትሯ ክልሎችም በየራሳቸው እየሰበሰቡ ያሉት ግብር ለውጥ ማምጣቱን አመላክተዋል፡፡
መደበኛውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወደ ታክስ ለማስገባት አሁንም በርካታ ሥራዎች እንደሚቀሩ በመጠቆም፤ ግዙፍ ኢኮኖሚን እየገነባች ያለች ሀገር ከዚህም በላይ ሀገራዊ የታክስ ገቢ የመሰብሰብ አቅምን ማሳደግ ይጠበቅባታል ነው ያሉት፡፡
በተያዘው የ2019 በጀት ዓመትም ከግብር 2 ነጥብ 83 ትሪሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን የተናገሩት ሚኒስትሯ፤ የሀገር ውስጥ ምርትን ከመነሻው በመከታተልና የገቢ ሸቀጦችን በማጥራት ከአምራቾች፣ አስመጪዎችና አከፋፋዮች ጋር በቅንጅት የሚሰራ እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡
