ይህን የገለጹት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ በኢትዮጵያ የኪርጊዝ ሪፐብሊክ አምባሳደር አዲልቤክ ቱልቴሚሮቭን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡
በውይይታቸው ሀገሪቱ በየዓመቱ ለወደብ ኪራይና ተያያዥ የሎጂስቲክስ አገልግሎቶች የምታወጣው ወጪ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ያስረዱት ምክትል ሰብሳቢው የባሕር በር ማግኘት እና አጋር ከሆኑ ሀገራት ጋር ቀጣናዊ የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ትስስር መፍጠር ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ህልውና እና ዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።
