የ28፣ 91፣ 182 እና 364 ቀናት ጊዜ ያላቸው እነዚህ የግምጃ ቤት ሰነዶች በሶስት ወራት ውስጥ ለገበያ የሚቀርቡ ሲሆን በአማካይ 9.2 በመቶ የወለድ መጠን የሚታሰብባቸው ናቸው፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መረጃ እነዚህ የመንግስት ግምጃ ቤት ሰነዶች እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በ7 ጊዜያት ለገበያ እንደሚቀርቡም ተጠቁሟል፡፡
የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጮቹ የመንግስትን የበጀት ጉድለት በሀገር ውስጥ ለመሙላት፣ የገንዘብ ህትመትን በመቀነስ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር እና ከብሔራዊ ባንክ ቀጥታ መበደርን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ያለሙ መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡
