ባለስልጣኑ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር የ2018 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ አተገባበር ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡
በዚህም ወቅት በበጀት አመቱ በ10 ሺህ 769 የማምረቻ ተቋማት፣ በ14 ሺህ 43 አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና በ11 ሺህ 435 የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ቁጥጥር መደረጉን ገልፆ ህጉን ላላከበሩ 1ሺ 496 ተቋማት ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አስታውቋል፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ በበጀት ዓመቱ የአካባቢ የህግ ማዕቀፍ፤ የአካባቢና ማህበረሰብ ተጽዕኖ አዋጅ እንዲሁም የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ በማዘጋጀት ተግባራዊ መደረጉን ነው የገለፁት፡፡
