EthiopiaNews

በ10 እና በ50 አባላት ንዑሳን ቡድኖች አጀንዳዎቻቸው ላይ ሲወያዩ የቆዩት ተመካካሪዎች ትናንት ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም 250 አባላት ላሉት ስልታዊ ቡድን ያጠናቀሩትን ሃሳብ ማቅረባቸውን የሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ይሄን ያለው የምክክሩ ሂደትን በተመለከተ ባወጣው አጭር መግለጫ ነው።

ኮሚሽኑ በምክክር ጉባኤው እየተሳተፉ ያሉ ተመካካሪዎች የምክክር ሂደቱ የሃሳብ ነፃነት የተከበረበት እንደሆነ መናገራቸውን አሳውቋል።

ሐምሌ 8 2018 አ.ም የተጀመረው የምክክር ጉባኤ ለ14 ኛ ቀናት በመካሄድ ላይ ነው።መረጃው ከኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተገኘ ነው።