EthiopiaNews

የአቢሲንያ ባንክ ወደ ገበያው መቀላቀል የግሉ ዘርፍ ተቋማት በሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያው ውስጥ የሚያደርጉት ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን የሚያሳይና ገበያውን የበለጠ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

በዚህም ለባለአክሲዮኖች እንዲሁም ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተጠቁሟል፡፡

በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ባንክ ገዥው ኢዮብ ተካልኝ የካፒታል ገበያው ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለኢንቨስትመንት መስፋፋት እና የረጅም ጊዜ ካፒታል ማሰባሰብን በመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል፡፡

እንደ ሀገር የካፒታል ገበያ አለመኖር ከፍተኛ ቁጭት ፈጥሮ መቆየቱን የጠቆሙት የብሄራዊ ባንክ ገዢው ይህንን ክፍተት ለመሙላት የካፒታል ገበያን በማቋቋም የተከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።