በስብሰባው መክፈቻ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቫር ጋቴቴ፣ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ኤድዋርድ ቢዚማ እንዲሁም የአባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።
ሚኒስትሮቹ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ቁልፍ አጀንዳዎችና የአፍሪካን አህጉራዊ ትስሰር ማፋጠን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል።
የአጀንዳ 2063 አፈፃፀም የሚከታተለውን ኮሚቴ ሪፖርት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት ስር ያሉ ስምምነቶችና የአሰራር ማዕቀፎች ያሉበት የትግበራ ደረጃም ይገመግማሉ፡፡
49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እስከ ነገ ይቆያልም ነው የተባለው።
