EthiopiaNews

የፌደራሉ የአቪዬሽን ደህንነት መስሪያ ቤት እንዳለው በአሜሪካ የተመዘገቡ 453 የሞዴሉ አውሮፕላኖች የወንበር አገጣጠም ችግር ያለባቸው ናቸው።

ወንበሮቹ የማሰሪያ ብሎናቸው ጠብቆ ባለመገጠሙ በአውሮፕላኑ በአደጋ ጊዜ አስተራረፍ ወቅት ወንበሮቹ ወልቀው መንገደኞችን ለአደጋ ሊያጋልጡ ይችላሉ።

እንዲህ ዓይነቱ የወንበር አገጣጠም አደጋ ቢያጋጥም መንገደኞቹን ከአውሮፕላኑ ለማውጣት የሚደረገውን የነፍስ አድን ሥራ ሊያስተጓጉለው ይችላል።

አሁን የአሜሪካው የአቪዬሽን ተቋም ያወጣው መመሪያ በሌሎች አገሮች አስገዳጅነት ባይኖረውም ብዙ አገሮች የአሜሪካውን ተቋም የቁጥጥርና ክትትል ሃሳብ ተግባሪዎች መሆናቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።