EthiopiaNews

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ይሄን ያስታወቀው ከውጭ ሀገር አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር ባካሄደው የምክክር መድረክ ላይ ነው።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዳንኤል ተሬሳ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከተከናወኑ ዋና ተግባራት መካከል የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት አዋጅን ወደ ሥራ ማስገባት ዋንኛው እንደሆነ ጠቅሰው አዋጁን ለማስፈፀም የሚያስችል መመሪያም በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው በተያዘው የ2019 በጀት ዓመትም የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል በስፋት የመላክ ዕቅድ መያዙን ገልፀው በዘርፉ የሚስተዋሉ ህገወጥ አሰራሮችን ለማስወገድ እንሰራለን ብለዋል፡፡

ዳንኤል ተሬሳ የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የዜጎችንና የሀገርን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸውን ጉልህ ድርሻ ተገንዝበው ሥራውን በኃላፊነትና በታማኝነት መፈፀም እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

አክለውም በኤጀንሲዎች መካከል የሚስተዋሉ ችግሮችን በውይይት መፍታት፣ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር ህገወጥ አሰራሮችን በጋራ መታገል እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡መረጃው ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።