EthiopiaNews

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፤ ባለፉት አምስት ዓመታት የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የላቀ ድርሻ እንዲኖረው የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ማሳየት መጀመራቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዚህ መሠረት በ2014 ዓ.ም ከዘርፉ የወጪ ንግድ ገቢ የተገኘውን 385 ሚሊዮን ዶላር በማሳደግ በ2018 በጀት ዓመት 607 ሚሊዮን ዶላር ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማጠናከር አዲስ የኤክስፖርት ስትራቴጂ እየተዘጋጀ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

በ2019 በጀት ዓመት ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የወጪ ንግድ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት መታወዱም ነው የተነገረው፡፡