የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክንደያ ገብረሕይወት መንግሥት ያደረገውን ርብርብ ተከትሎ ተማሪዎቹ ወደ ፈተና አዳራሾች ገብተዋል ብለዋል፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ በበኩላቸው፤ የፈተናው መጀመር በክልሉ የሚገኙ ወጣቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲቃና እና ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል፡፡
ለፈተናው ስኬት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ በማከናወን ተማሪዎቹ ያለምንም እንግልትና ስጋት ፈተናቸውን እንዲወስዱ የጸጥታና የትምህርት ባለሙያዎች የተቀናጀ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛልም ነው የተባለው፡፡
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መርሐ ግብር 30 ሺህ የሚጠጉ የክልሉ ተማሪዎች በአዲስ አበባ፣ በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በወረቀትና በበይነ መረብ ፈተናውን እንደሚወስዱ ተመላክቷል።
